No products in the cart.

Contacts

92 Bowery St., NY 10013

thepascal@mail.com

+1 800 123 456 789

Category: COVID-19

COVID-19

What do you think should be the role of EOTC in COVID-19 Prevention?

የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. በኮቪድ-19 መከላከል ዙሪያ ሊኖራት የሚገባው ሚና ምንድን ነው ብለው ያምናሉ?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ብፁዓን አባቶች፤ የሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፤ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ውጤታማ የሆነ ውይይት በኮቪድ-19 ዙሪያ አድርጓል። የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. በኮቪድ-19 መከላከል ዙሪያ የሚኖራትን አስተዋጾ (The role of EOTC in COVID-19 prevention) በመዳሰስ እስከ አሁን የተደረጉትንና ወደፊትም ሊደረጉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል። የመከላክል እርምጃዎችን ቤተክርስቲያንና ምዕመናን በመተባበር ተፈፃሚ ማድረግ እንደሚገባቸው፤ እንዲሁም የክትባት ተደራሽነት እንዲጨምርና ምዕመናን በተለያዩ የሀሰት አሉባልታዎች እንዳይደናገሩና ከጤና ባለሙያዎች ብቻ በሚሰጣቸው መረጃ በመጠቀም እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከዚህ አስከፊ በሽታ እንዲጠብቁ አፅንዎት ሰጥተዋል። በዚህም ውይይት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዲሲ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የሰሜን ካሊፎርኒያ የኔቫዳ እና የአሪዞና አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በመገኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የጀመረውን አገልግሎቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበው አባታዊ ምክርን እንዲሁም ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።