የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. በኮቪድ-19 መከላከል ዙሪያ ሊኖራት የሚገባው ሚና ምንድን ነው ብለው ያምናሉ?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ብፁዓን አባቶች፤ የሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፤ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ውጤታማ የሆነ ውይይት በኮቪድ-19 ዙሪያ አድርጓል። የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. በኮቪድ-19 መከላከል ዙሪያ የሚኖራትን አስተዋጾ (The role of EOTC in COVID-19 prevention) በመዳሰስ እስከ አሁን የተደረጉትንና ወደፊትም ሊደረጉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል። የመከላክል እርምጃዎችን ቤተክርስቲያንና ምዕመናን በመተባበር ተፈፃሚ ማድረግ እንደሚገባቸው፤ እንዲሁም የክትባት ተደራሽነት እንዲጨምርና ምዕመናን በተለያዩ የሀሰት አሉባልታዎች እንዳይደናገሩና ከጤና ባለሙያዎች ብቻ በሚሰጣቸው መረጃ በመጠቀም እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከዚህ አስከፊ በሽታ እንዲጠብቁ አፅንዎት ሰጥተዋል። በዚህም ውይይት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዲሲ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የሰሜን ካሊፎርኒያ የኔቫዳ እና የአሪዞና አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በመገኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የጀመረውን አገልግሎቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበው አባታዊ ምክርን እንዲሁም ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።
Thanks Dr Yared! Yes religious leaders can play a key role in stopping and spreading COVD by teaching their follower about spread awareness and needed protection against COVID-19
Thank you for sharing the news. This is a great start.
Great discussion point. Keep doing the good work!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር በኮቪድ-19 መከላከል ላይ የሚሰጠው ትኩረት በቅድሚያ የሰዎችን ጤንነት በመጠበቅ ላይ መሆን አለበት። የህ ሲባል የጤና ማስተዋወቅ መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች ጤናማ ባህሪዎችን እንዲመርጡ እና እንዲሳተፉ ማድረግ ። በተጨማሪም ጤናማ የአንዋኗር ዘይበዎቼን በመከተል አና በማዳበር አደጋን የሚቀንሱ ለውጦችን አንድያመጡ ማገዝ። በኮቪድ-19 የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ የሚሆነው በተጨናነቁ እና በቂ አየር በሌለባቸው ቦታዎች ላይ በበሽታው የተጠቁ ሰዎች በቅርብ ጊዜ አብረው የሚያሳልፉበት ነው። ሰዎች በተሰበሰቡባቸው ቦታዎች፣ ብዙ ጊዜ በተጨናነቀ የቤት ውስጥ ቦታዎች እና ጮክ ብለው በሚናገሩበት፣ በሚጮሁበት፣ በትነንፈሳቸው በሚዘፍኑበት ወይም እንደ ምግብ ቤቶች፣ የመዘምራን ልምምዶች፣ የአካል ብቃት ክፍሎች፣ የምሽት ክበቦች፣ ቢሮዎች እና የአምልኮ ቦታዎች ወረርሽኙ ተዘግቧል። የቤተክርስቲያናችንን አካባቢ በተቻለ መጠን አስተማማኝ ለማድረግ፡-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር የግል መከላከያ መሣሪያዎችን ማቅረብ፣የምናገለገልላቸው ሰዎች በቀላሉ ሰለ ኮቪድ-19 መከላከል መረጃ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ወየም መረጃ በቀላሉ ሊያገኙበት የሚችሉበትን መረብ ሥራ ወይም ፕላትፎርም መፍጠር ይኖርበታል።